የዒድ አል አድሃ (አረፋ) በዓል በጅግጅጋ ከተማ ተከበረ
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 21፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) 1 ሺህ 444ኛው የዒድ አል አድሃ (አረፋ) በዓል በሶማሌ ክልል ጅግጅጋ ከተማ ተከብሯል፡፡
በዓሉ በእስልምና እምነት ተከታዮች ዘንድ በተለያዩ ሃይማኖታዊ ስነ-ስርዓቶች ነው የተከበረው፡፡
በአከባበር ስነ-ስርዓቱ ሰላት እና ተክቢራን ጨምሮ የተለያዩ ሃይማኖታዊ ስነ-ስርዓቶች ተከናውነዋል፡፡
በስነ ስርዓቱ ላይ የተገኙት የክልሉ ርዕሰ-መስተዳድር ሙስጠፌ መሐመድ÷ ሕዝብ ሙስሊሙ በዓሉን ሲያከብር ሰላሙን በመጠበቅ እና አንድነቱን በሚያጠናክሩ ተግባራት መሆን እንዳለበት ገልጸዋል።
የክልሉ ሕዝብ ለዘመናት ያዳበረውን በሰላም አብሮ የመኖር ባህሉን መጠበቅ እንደሚኖርበት አመልክተዋል።
ለዚህም በዓሉን አብሮ በማሳለፍ ለዘመናት ያጎለበተውን ማህበራዊ መስተጋብር በይበልጥ አጠናክሮ ማስቀጠል እንዳለበትም ነው ርዕሰ መስተዳድሩ ያመለከቱት።