Fana: At a Speed of Life!

የነገውን የሕዝብ ውይይት ለመምራት ከፍተኛ አመራሮች ሆሳዕና ገቡ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 6፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ነገ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የሚካሔዱትን ሕዝባዊ ውይይቶች ለመምራት ከፍተኛ የመንግሥት ሥራ ኃላፊዎች ሆሳዕና ከተማ ገብተዋል፡፡

በነገው ዕለት “ኅብረ ብሔራዊ ወንድማማችነትና እህትማማችነት ለዘላቂ ሰላምና ሁለንተናዊ ብልጽግና”በሚል መሪ ሐሳብ በ20 ከተሞች ሕዝባዊ ውይይቶች ይካሄዳሉ፡፡

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልልም በሆሳዕና እና ወልቂጤ ከተሞች ሕዝባዊ የውይይት መድረኮች እንደሚካሄዱ ተገልጿል፡፡

ለዚህም የብልጽግና ፓርቲ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል የሆኑት ፍቃዱ ተሰማ እና ሞገስ ባልቻ ሆሳዕና ከተማ መግባታቸውን የክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ መረጃ አመላክቷል፡፡

አመራሮቹ ሆሳዕና ሲገቡ በብልጽግና ፓርቲ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ዲላሞ ኦቶሬ (ዶ/ር) እና ምክትል ርዕሰ መሥተዳድር አንተነህ ፍቃዱን ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች አቀባበል አድርገውላቸዋል።

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.