Fana: At a Speed of Life!

በክልሉ ከ6 ሺህ በላይ መምህራን የብቃት መመዘኛ ፈተና እየወሰዱ ነው

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 24፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ከ6 ሺህ 700 በላይ ለሚሆኑ መምህራን የብቃት መመዘኛ ፈተና እየተሰጠ ነው።

የክልሉ የትምህርት ቢሮ ኃላፊ አቶ አልማው ዘውዴ÷የምዘና ፈተናው ለአንደኛ ደረጃ መምህራን፣ ርዕሰ መምህራንና ሱፐርቫይዘሮች እየተሰጠ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

በትምህርት ዘርፍ የገጠመውን የትምህርት ስብራት ለማሻሻል ከሚሰሩ ቁልፍ ተግባራት አንዱ የመምህራን ብቃት ደረጃ ማሳደግ ትልቅ ድርሻ እንዳለውም አስረድተዋል፡፡

ምዘናው የመምህራንና የትምህርት ቤት አመራሮችን ሙያዊ ብቃት ደረጃን በጠበቀ የምዘና ስርዓት ውስጥ እንዲያልፉ ለማድረግ ያለመ መሆኑን ገልጸዋል።

ይህም ብቃት ያላቸው የመምህራን እና የትምህርት ቤት አመራሮችን በማፍራት ጥራት ያለው ትምህርት ለማስተማር ድርሻው የጎላ መሆኑን አብራርተዋል።

ምዘናው በ7 የትምህርት ዓይነቶች አስቀድሞ ለተመዘገቡ ተመዛኞች እየተሰጠ እንደሆነና ምዘናው በቀጣይ ከመምህራን ጥቅማጥቅምና ደረጃ እድገት ጋር በሚገናኝ መልኩ የሚሰራ መሆኑን የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.