በመዲናዋ በተካሄደው የምክክር ምዕራፍ የተሳተፉ አካላት እነማን ናቸው?
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 28፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በአዲስ አበባ ከተማ ባካሄደው የአጀንዳ ልየታ ምክክር ምዕራፍ ላይ ሕብርተሰብ ተወካዮች፣ ተቋማት፣ ማኅበራት፣ የፖለቲካ ፓርቲ ተወካዮች፣ የመንግሥት አካላት ተወካዮች እና ሌሎች ተሳትፈዋል፡፡
- 121 የተለያዩ የሕብረተሰብ ክፍል ተወካዮች
- 228 የተቋማት እና የማኅበራት ተወካዮች
- 52 የፖለቲካ ፓርቲ ተወካዮች
- 128 የመንግስት አካላት ተወካዮች
- 100 ተፅዕኖ ፈጣሪ ግለሰቦች
- 16 የፖለቲካ ፓርቲዎች
- 11 ሞደሬተሮች (ውይይቶቹን በማስተባበር) ተሳትፈዋል።
እነዚህ ባለድርሻ አካላት በቡድን የተወያዩባቸውን አጀንዳዎች ግንቦት 26 ቀን 2016 ዓ.ም ለተወካዮቻቸው ሰጥተዋል፡፡
በሂደቱ ሁሉም ተወካዮች በሞደሬተሮች አጋዥነት አጀንዳዎችን አደራጅተዋል፡፡
ግንቦት 27 ቀን 2016 ዓ.ም የአምስቱ ባለድርሻ አካላት ተወካዮች አጀንዳቸውን ለኮሚሽኑ አቅርበዋል፡፡
ኢትዮጵያ እየመከረች ነው!