Fana: At a Speed of Life!

በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የሴቶችን ተሳትፎ ለማሳደግ እየተሰራ ነው – ብልፅግና ፓርቲ

አዲስ አበባ፣ ጥር 4፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የብልፅግና ፓርቲ በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ላይ የሴቶችን ተሳትፎ ለማሳደግ እየተሰራ ነው አለ።
የፓርቲው የሴቶች ክንፍ ምክር ቤት ባለፉት ስድስት ወራት የተሰሩ ስራዎችን ገምግሟል።
የብልፅግና ፓርቲ የሴቶች ክንፍ ምክትል ፕሬዚዳንት መስከረም አበበ በዚህ ወቅት እንዳሉት÷ ዘንድሮ በሚካሄደው 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ላይ የሴቶችን ተሳትፎ ለማሳደግ እየተሰራ ይገኛል።
ከጥር 12 እስከ የካቲት 12 ቀን 2018 ዓ.ም በሴቶች ተሳትፎ የፀናች ኢትዮጵያ በሚል የአንድ ወር ንቅናቄ እንደሚካሄድም ገልጸዋል።
በንቅናቄው የሴቶችን ኢኮኖሚያዊ፣ ማሕበራዊና ፖለቲካዊ ተሳትፎ ከፍ ለማድረግ ይሰራልም ነው ያሉት።
በቅድስት ተስፋዬ
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.