ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) ለጅቡቲ ፕሬዚዳንት ኢስማኤል ኦማር ጊሌ እና ለሶማሊያ ፕሬዚዳንት ሐሰን ሸክ ሞሃሙድ አቀባበል አደረጉ
አዲስ አበባ፣ ጥር 23፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ለጅቡቲ ፕሬዚዳንት ኢስማኤል ኦማር ጊሌ እና ለሶማሊያ ፕሬዚዳንት ሐሰን ሸክ ሞሃሙድ አቀባበል አድርገውላቸዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለመሪዎች አቀባበል ያደረጉት ዛሬ ጠዋት በጅግጅጋ አውሮፕላን ማረፊያ መሆኑን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት አስታውቋል።