ካፒቴን ቃልኪዳን ግርማ የኤርባስ ኤ – 350 ዋና አብራሪነት ማዕረግን በማግኘት የመጀመሪያዋ ኢትዮጵያዊት ሴት ሆነች
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 11፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ካፒቴን ቃልኪዳን ግርማ በኢትዮጵያ አየር መንገድ የኤርባስ ኤ – 350 ዋና አብራሪነት ማዕረግን በማግኘት የመጀመሪያዋ ኢትዮጵያዊት ሴት አብራሪ ሆነች።
አየር መንገዱ ካፒቴን ቃል ኪዳን ለደረሰችበት ስኬት የእንኳን ደስ አለሽ መልዕክት አስተላልፏል።
ካፒቴን ቃልኪዳን ግርማ ከዚህ ቀደም ቦይንግ 737 አውሮፕላንን በዋና አብራሪነት ስታበር መቆየቷን አየር መንገዱ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ገልጿል፡፡
አሁን ላይም ዘመናዊውን ኤርባስ ኤ 350ን በዋና አብራሪነት እንድታበር ማዕረጉን ማግኘቷንም ነው የገለጸው፡፡
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሙሉ በሙሉ በሴቶች የተመራ በረራ ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ ዋሺንግተን ዲሲ፣ ኦስሎ እና ሌሎች ከተሞች ማድረጉ የሚታወስ ነው።
በወቅቱ በአብራሪነት፣ በበረራ አስተናጋጅነት፣ በበረራ ምህንድስ እና በሌሎች ዘርፎች ሙሉ በሙሉ ሴቶች የተሳተፉበት በረራ ማካሄዱም ይታወሳል።