የምስራቅ አፍሪካ ተጠባባቂ ኃይል አባላቱን አሰልጥኖ አስመረቀ
አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 12፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)የምስራቅ አፍሪካ ተጠባባቂ ሃይል በጥምር ውጊያና ድጋፍ አሰጣጥ ኮርስ ከ10 ሃገራት የተውጣጡ አባላቱን አሰልጥኖ አስመርቋል።
የመከላከያ የውጭ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ተወካይ ብርጋዴር ጀኔራል ጥላሁን አሸናፊ ስልጠናው የምስራቅ አፍሪካ ሀገራትን ሰላም እና የተረጋጋ ለማድረግ ከፍተኛ ሚና ይኖረዋል ብለዋል ፡፡
በስልጠናው የተገኘውን አቅም በማጎልበትና ተቀናጅቶ በመስራትም ቀጣናውን ከግጭት የፀዳ ማድረግ እንደሚገባም ገልጸዋል።
የስልጠናው ተሳታፊዎች በበኩላቸው በስልጠናው ያገኙትን አቅም በተግባር አውለው በቀጠናው ሰላም ለማስፈንና ቀጠናዊ መረጃዎችን በማጋራት የጋራ ግብን ለማሳካት በጋራ እንደሚሰሩ መናገራቸውን ከመከላከያ ሰራዊት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!