በወረኢሉ፣ በሚሌና በከሚሴ ግንባር ጠላት ኪሳራ እየደረሰበት ነው – የመንግስት ኮሙኒኬሽን
አዲስ አበባ ፣ ህዳር 9 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) አገራዊ ሉዓላዊነትን ለማስከበር ህዝቡ ተሳትፎውን አጠናክሮ መቀጠሉን የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት አስታወቀ።
የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዶክተር ለገሰ ቱሉ መግለጫ ሰጥተዋል።
በመግለጫቸው በሺህዎች የሚቆጠሩ የቀድሞ ሰራዊት አባላት ወደ ግንባር መጓዛቸውን እና ህዝቡም ደጀንነቱን አጠናክሮ መቀጠሉንም ገልጸዋል።
የመንግስት የስራ ሃላፊዎችም በመሪነት፣ በግንባርና በደጀንነት እየተንቀሳቀሱ መሆናቸውን ጠቅሰዋል።
በሳምንቱ በሺህዎች የሚቆጠሩ የጦር መሳሪያዎች እና ህገወጥ ገንዘብ መያዙን እንዲሁም ትጥቆችና ዩኒፎርሞች መገኘታቸውን አስረድተዋል።
ከዚህ ጋር ተያይዞ በተካሄደ ፍተሻ ዝቅተኛ ገቢ ካላቸው ግለሰቦች በሂሳብ ቁጥራቸው እስከ 80 ሚሊየን ብር መገኘቱንም ነው የገለፁት።
ህዝቡና የፀጥታ ሀይሉ በቅንጅት በመስራታቸው አገር ላይ የተደገሰን ጥፋት እንዳጋለጠ አንስተዋል።
አሸባሪ ቡድኑና የጥፋት ሀይሉ በህዝቡና በመንግስት መለያየትን ለማምጣት የሀሰት ፕሮፖጋንዳ በመንዛት ላይ መሆናቸውንም ጠቁመዋል።
ከአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ጋር ተያይዞም ለአሸባሪዎቹ ህወሓትና ሸኔ ድጋፍ በማድረግ የተጠረጠሩ ግለሰቦች እንጅ ብሔርን መሰረት ያደረገ እስራት አለመፈጸሙን አስረድተዋል።
በአዲስ አበባ ከተማ ከግማሽ ሚሊየን በላይ የትግራይ ተወላጆ እንደሚኖሩ ይገመታል ያሉት ዶክተር ለገሰ የታሰሩት ከአንድ ሺህ የማይበልጡ መሆናቸውንም አክለዋል።
በወረኢሉ፣ በሚሌና በከሚሴ ግንባር ጠላት ኪሳራ እየደረሰበት እንደሆነም ሚኒስትሩ በመግለጫቸው ጠቁመዋል።
በግንባር ከ10 ሺህ እስከ 15 ሺህ የሚደርሱ ወታደሮች መርገፋቸውን እና የሽብር ቡድኑ ክፍለ ጦሮች መፍረሳቸውንም ጠቅሰዋል።
ከዚህ ባለፈም በሽብር ቡድኑ ሸኔ ላይ በምዕራብ ሸዋና በወለጋ እርምጃ እየተወሰደ መሆኑን ጠቁመው፥ ለዚህም የኦሮሞ ወጣቶች እያሳዩ ያሉት ድጋፍ የሚበረታታ መሆኑን አውስተዋል።
በአፈወርቅ እያዩ እና በርናባስ ተስፋዬ
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!