አንድ ብር እስኪቀረኝ የመከላከያ ሰራዊቱንና ሌሎች የጸጥታ ሀይሎችን እደግፋለሁ
አዲስ አበባ፣ ህዳር 20፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) “አንድ ብር እስኪቀረኝ ድረስ የአገር መከላከያ ሰራዊቱንና ሌሎች የጸጥታ ሀይሎችን እደግፋለሁ” ሲሉ ባለሀብቷ ወይዘሮ ትልቅሰው ገዳሙ ገለጹ።
ወይዘሮ ትልቅሰው ገዳሙ የጠቅላይ ሚኒስትሩን ጥሪ በመቀበል ግንባር ተገኝተው ለጸጥታ ሀይሉ የምግብና አልባሳት ድጋፍ አድርገዋል።
ድጋፉን ሲያስረክቡ እንዳሉት፤ ከሌሎች ባለሀብቶች ጋር በመሆን በተለያዩ ግንባሮች ለጸጥታ ሀይሉ በሚሊዮኖች የሚቆጠር ድጋፍ አድርገዋል።
በዛሬው እለትም ሰንጋዎችን ጨምሮ የእለት ደራሽ የሚሆን እንጀራና የሴቶች የንጽሕና መጠበቂያና አልባሳት ድጋፍ ማድረጋቸውን ገልጸዋል።
“ሀገር ሰላም ስታጣ ምን ያህል እንደተረበሽን በጥቂት ቀናት በነበረው ክስተት አይተናል፣ ለዚህ የሰላም ዘብ ደግሞ ማንኛውንም ድጋፍ ማድረግ ይጠበቅብናል” ብለዋል።
በቀጣይም አንድ ብር እስኪቀረኝ ድረስ ለመከላከያ ሰራዊቱና ለጸጥታ ሀይሉ ድጋፍ ማድረጌን እቀጥላለሁ ብለዋል።
በዘላለም ገበየሁ
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!