Fana: At a Speed of Life!

የአረንጓዴ አሻራቸውን ማኖሪያ ፓርክ በዳያስፖራው ማህበረሰብ ስም ሰይመናል- ከንቲባ አዳነች አቤቤ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 26፣2014 (ኤፍ ቢ ሲ)  ዛሬ በማለዳው የአረንጓዴ አሻራቸውን ማኖሪያ ፓርክ በዳያስፖራው ማህበረሰብ ስም ሰይመናል ሲሉ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ፡፡

ከንቲባዋ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሁፍ÷ በጠቅላይ ሚኒስትራችን አነሳሽነት የተጀመረው ኢትዮጵያችንን አረንጓዴ የማልበስ ተግባር የሁሉም ኢትዮጵያዊ ሃላፊነት ነው ብለዋል።

ፓርኩ ትርጉሙ ከአረንጓዴ ልማት በላይ ነውም ሲሉ ከንቲባዋ ገልጸዋል፡፡

በውጭው ዓለም ኢትዮጵያ ጫና ሲደርስባት ዳያስፖራው አቅሙን ሳይሰስት ትግል ሲያደርግ ቆይቷልም ነው ያሉት።

ትውልድ እንዲማርና ወቅቱን እንዲያስብ እንዲሁም አካባቢን ለማልማት ለዳያስፖራው ማስታወሻ የሚሆንም ነው ብለዋል።

የዳያስፖራው የአረንጓዴ አሻራ ተሳትፎንም ያበረታታል ፣ በቀጣይም መሰል ተሳትፎዎችን በማጉላት አገርን በሁሉም መስክ ለመደገፍ የበኩላቸውን አስተዋጽኦ እንደሚወጡ ተስፋ አደርጋለሁ ሲሉ ገልጸዋል ።

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.