Fana: At a Speed of Life!

ሊከፋፍሉንና ሊያዳክሙን የሚችሉ ሀሳቦችን ወደ ጎን ማቆየት ይገባናል – ዶክተር ይልቃል ከፍያለ

አዲስ አበባ፣ ጥር 3 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአማራ ህዝብ ሊከፋፈሉትና ሊያዳክሙት የሚችሉ ሃሳቦችን ወደ ጎን በማቆየት ራሱን ከሌላ ወረራ ሊጠብቅ እንደሚገባ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ይልቃል ከፍያለ አሳሰቡ።
ርዕሰ መስተዳድሩ አሸባሪው ህወሃት በአማራ ክልል ላይ ያደረሰውን ውድመት ሰሞኑን ምልከታ ላደረጉ የመገናኘ ብዙሃን ማብራሪያ በሰጡበት ወቅት ክሳቸው ስለተቋረጠ የህወሓት አመራሮችም አንስተዋል።
ርእሰ መስተዳድሩ ዶክተር ይልቃል ከፍያለ፥ አመራሮቹ የአማራን ህዝብ ጠላት አድርገው በመሳል ባለፉት በርካታ አመታት በህይወት፣ በንብረትና በስነ ልቦናው ላይ በደል እንዲደርስበት በማድረጋቸው ህዝቡ በአመራሮቹ መፈታት ላይ ቅሬታ ቢይዝ እውነት አለው ብለዋል።
የአማራ ህዝብ በተከታታይ ሲደርስበት የነበረው በደል በእነዚህ ሰዎች ጠንሳሽነት እንደነበር ለአፍታም አንዘነጋም ያሉት ርዕሰ መስተዳደሩ፥ ነገር ግን አሁን ማየት ያለብን እና ጠቃሚ የሚሆነው የሰዎቹ መፈታት አለመፈታትን ሳይሆን ሊከፋፍሉንና ሊያዳክሙን የሚችሉ ሀሳቦችን ወደ ጎን በማቆየት በዋና ዓላማችንና መርሃችን ላይ አተኩረን አንድነታችንን መጠበቅ ነው ብለዋል።
የእነስብሃት ነጋ መፈታት አለመፈታት ላይ አተኩረን ከተለያየን እንዳከማለን፤ ለሌላ ጥቃት እንጋለጣለን ሲሉ አስጠንቅቀዋል።
ስለሆነም ለእኛ እንደ አማራ ክልል የሚጠቅመው መርሃችን ላይ ትኩረት በማድረግ አንድነትን በማጠናከር ሊመጣ ከሚችል ዳግም ወረራ ራሳችንን መጠበቅ ነው ያሉት።
በሀይለየሱስ ስዩም
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.