Fana: At a Speed of Life!

በቤንሻንጉል ጉሙዝ ከ44 ሺህ በላይ ሄክታር መሬት ላይ የአፈርና ውሃ ጥበቃ ሥራዎች ይከናወናሉ

አዲስ አበባ ጥር 3፣2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል በበጋ ወራት ከ44 ሺህ በላይ ሄክታር መሬት ላይ የአፈርና ውሃ ጥበቃ ስራዎች እንደሚከናወኑ ተገለፀ፡፡

“የአየር ንብረት ለውጥ እና ህልውናችን በተባበረ ክንድ” በሚል መሪ ቃል በአሶሳ ከተማ መገሌ ቀበሌ ክልላዊ የአፈርና ውሃ ጥበቃ ሥራዎች ማስጀመሪያ መርሀ ግብር ተካሂዷል፡፡

“እያጋጠሙን ያሉ የፀጥታ ችግሮችን በመመከት የልማት ሥራዎችን በተደራጀ መልኩ ማከናወን ይገባል” ሲሉ በመርሀ ግብሩ ላይ የተገኙት የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ጌታሁን አብዲሳ ተናግረዋል፡፡
የአፈርና ውሃ ጥበቃ ሥራዎች የመሬት ለምነት እንዲጨምር ፋይዳቸው የላቀ በመሆኑ የክልሉ መንግስት ሥራውን በልዩ ትኩረት እንደሚመራው ነው ያስታወቁት፡፡
ሀገራት በዕርዳታ ስም የሀገር ሉዓላዊነትን እየተጋፉ ስለሆነ ኢትዮጵያ የምግብ ዋስትናዋን በዘላቂነት ማረጋገጥን የሉዓላዊነቷ ቁልፍ ጉዳይ አድርጋ መሥራት ላይ እንደምትገኝ በግብርና ሚኒስቴር የተፈጥሮ ሀብት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ፕሮፌሰር እያሱ ተናግረዋል፡፡
በግጭቱ ምክንያት ከቤት ንብረታቸው ተፈናቅለው በችግር ላይ ያሉ ዜጎች እንዲቋቋሙ ሁሉም የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣም ጠይቀዋል፡፡
በክልሉ ከ44 ሺህ 300 በላይ ሄክታር መሬት ላይ የአፈርና ውሃ ጥበቃ ሥራዎች ይሰራሉ ያሉት የክልሉ ግብርናና ተፈጥሮ ሀብት ቢሮ ሃላፊ ባበክር ኸሊፋ ዕቅዱን ለማሳካት ትኩረት ተደርጎ ይሰራል ብለዋል፡፡
ሁሉም ወረዳዎች የአፈርና ውሃ ጥበቃ ስራዎችን በተደራጀ መልኩ እንዲያስቀጥሉም የቢሮ ኃላፊው ጥሪ አቅርበዋል፡፡
በአሶሳ በተጀመረው የአፈርና ውሃ ጥበቃ ሥራ ማስጀመሪያ መርሀ ግብር ላይ የተሳተፉ አርሶ አደሮች÷ ከዚህ በፊት በተከናወኑ የአፈርና ውሃ ጥበቃ ስራዎች ተጠቃሚ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡
አርሶ አደሮቹ የተገኘውን ልምድ በማስቀጠል ለም መሬትን ለቀጣዩ ትውልድ የማስተላለፍ ኃላፊነታቸውን እንደሚወጡ መግለጻቸውን ከክልሉ ኮሙዩኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.