Fana: At a Speed of Life!

የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፌ ሙሁመድ ከፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ ጥር 3፣2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እና የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች አዲሱን የሀገር መከላከያ ዋና መስሪያ ቤትን በመጎብኘት ከፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ጋር ተወያይተዋል፡፡
በጉብኝቱ ላይ ከርዕሰ መስተዳድሩ በተጨማሪ የሶማሌ ክልል ብልፅግና ጽ/ቤት ኃላፊ ኢ/ር መሀመድ ሻሌ፣ የክልሉ የሰላምና ደህንነት ቢሮ ኃላፊ አቶ ሙበሽር ዱባድ፣ የፕሬዝደንት ጽ/ቤት ኃላፊ ዶ/ር ሁሴን ሃሺ እና የሶማሌ ክልል ልዩ ኃይል አዛዥ ኮሚሽነር መሀመድ አህመድ ተገኝተዋል፡፡
ርዕሰ መስተዳድሩ እና ልኡካቸው ከፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ጋር በአፍሪካ ቀንድ፣ በሀገሪቱ እና በክልሉ ስላለው የጸጥታ ጉዳይ ጠቃሚ ውይይት ማድረጋቸውን የክልሉ የሰላምና ደህንነት ቢሮ ኃላፊ አቶ ሙበሽር መግለጻቸውን ከክልሉ መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን
May be an image of 6 people and people standing
0
People reached
0
Engagements
Distribution score
Boost post
Like

Comment
Share
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.