Fana: At a Speed of Life!

የክልል ርዕሳነ መስተዳድራንና መንግስታት ለጥምቀት በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ

አዲስ አበባ፣ ጥር 10፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የክልል ርዕሳነ መስተዳድራንና መንግስታት የጥምቀት በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።
በዚህም የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ርዕሰ መስተዳደር አቶ ሽመልስ አብዲሳ፥ ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች ባስተላለፉት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት ጥምቀት ለሰው ልጆች በሙሉ ትልቅ አስተምህሮ እንዳለው አንስተዋል።
አማኞች የጥምቀትን በዓል ታሳቢ በማድረግ በጥምቀቱ ይቅርታን፣ ሰላምን፣ መተሳሰብን፣ አንድነትን፣ አዲስ ተስፋና ህይወትን ለመማማር በህብረት በዓሉን እንደሚታደሙ ነው ያመለከቱት።
ነገር ግን ሀጢያትንና ክፋትን የተለማመዱ እኩያን ለክፋት ሊሰማሩ ስለሚችሉ ምእመናን አጠራጣሪ እንቅስቃሴዎችን ባዩ ጊዜ ለጸጥታ ሀይሎች ጥቆማ በማድረግ ለበዓሉ ሰላምና ድምቀት የበኩላቸውን ድርሻ እንዲወጡ አሳስበዋል።
የአማራ ክልል ርዕሰ መስተደድር ይልቃል ከፋለ ለክርስትና ዕምነት ተከታዮች ባስተላለፉት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት በዓሉን ለመታደም በርካቶች በጎንደር ከተማ መገኘታቸውን ገልፀው ይህም የክልሉ ሰላም እየተረጋገጠ መሆኑንና የቱሪዝም ዘርፉ መነቃቃቱን ማሳያ ነው ብለዋል፡፡
በተመሳሳይም የደቡብ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ርስቱ ይርዳ ፥ለክርስትና እምነት ተከታዮች የጥምቀትን በዓል ምክንያት በማድረግ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።
አቶ ርስቱ ህብረተሰቡ በዓሉን ሲያከብር እንደ ከዚህ ቀደሙ ሁሉ የመረዳዳት እና የመደጋገፍ ባህሉን በማጠናከር ሊሆን ይገባል ብለዋል።
በጥምቀት በዓል መተዋወቅ፣ መግባባት፣ ሀገራዊ አንድነት ይበልጥ የሚንጸባረቅበት በመሆኑ አሁን ላጋጠመን ፈተና ሁነኛ መፍትሄ ለማበጀት ምክንያት ይሆናልም ነው ያሉት።
በዓልሉን በሞቀ ቤታችን ስናከብር ያለ ሀጥያታቸው በአሸባሪው ህወሃት በግፍ ተፈናቅለው በማይመች ሁኔታ ላይ ሆነው የሚያከብሩ ወገኖቻችንን ልናስብ ይገባል ሲሉም ርዕሰ መስተዳድሩ በመልዕክታቸው ተናግረዋል።
የሀረሪ ክልላዊ መንግስት በበኩሉ ፥ የክልሉ ህዝብ ለዘመናት በሰላም፣ በፍቅር፣ በመከባበር እና በአብሮነት የኖረና ለሌሎች አካባቢዎችም ምሳሌ የሚሆን የድንቅ እሴት ባለቤት መሆኑን አንስቷል።
ህዝበ ክርስትያኑ በዓሉን ሲያከብር ይህንን በማንፀባረቅ የተቸገሩ ወገኖች በመርዳት፣ የተራቡትን በማብላት የተጠሙ ወገኖችን በማጠጣት እንዲሁም በጦርነቱ ምክንያት የተፈናቀሉ ወገኖችን በመደገፍ እንደሚያሳልፍ እንደሚተማመን ነው ያስታወቀው።
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፤ እንገንባ፤ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
0
People reached
0
Engagements
Boost post
Like

 

Comment
Share
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.