የአምራች ኢንዱስትሪውን የገበያ ችግር ለመቅረፍ የሚያስችል ስምምነት ተፈረመ
አዲስ አበባ፣ ጥር 13፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር በአምራች ኢንዱስትሪው ዘርፍ ያለውን የግብዓት አቅርቦት እና የገበያ እጥረት ችግር ለመፍታት የሚያስችል ስምምነት ከጅቲኤስ ኃ/የተ/የግል ድርጅት ጋር ተፈረመ፡፡
ስምምነቱ የአምራች ኢንዱስትሪውን የግብዓት አቅርቦትና የምርት ገበያ እጥረት በመቅረፍ በአቅራቢዎችና ገዢዎች መካከል ያለውን ክፍተት የሚሞላና በአንድ ማዕከል በማገናኘት ትስስራቸውን የሚያጠናክር መሆኑ ተገልጿል፡፡
ቀጣይነት ያለው እና ተወዳዳሪ የሆነ ከፍተኛ፣ መካከለኛና አነስተኛ አምራች ኢንዱስትሪን ለመገንባትና ለማሳደግ በዲጂታል ገበያ ተወዳዳሪ ለመሆን ያግዛልም ነው የተባለው፡፡
በስምምነቱ አምራች ኢንዱስትሪውን በኦንላይን የማስተዋወቅና የማበረታታት፣ የማስተባበር፣ ስልጠና የመስጠት እንዲሁም የአምራች መረጃ የመለዋወጥ ስራ ይሰራልም ተብሏል፡፡
ጅቲኤስ ትሬድንግ ኃላፊነቱ የተወሰ የግል ድርጅት “አምራች ዶት ኔት” የተሰኘ በ2005 ዓ.ም የተመሠረተ በኦንላይን የመገበያያ ማዕከል ሲሆን ፥ አምራቾችን፣ ግብዓት አቅራቢዎችንና ገዢዎችን በአንድ ማዕከል በዲጂታል ገበያ የሚያገናኝ ድርጅት መሆኑ ተገልጿል፡፡
በማምረቻው ዘርፍ ያለውን የተበጣጠሰ ገበያ ወደ አንድ ማዕከል በማምጣት በኦንላይን ገዢና ሻጭን በማገናኘት የሀገር ውስጥም ሆነ ዓለም አቀፍ የገበያ ትስስር የሚፈጥር በመሆኑ ለአምራቾች ከፍተኛ ጠቀሜታ እንዳለው ከኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!