Fana: At a Speed of Life!

በደቡብ ክልል ከ3 ቢሊየን ብር በላይ ወጪ ልዩ ልዩ የ ፕሮጀክቶች ግንባታ እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ ጥር 16፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በደቡብ ክልል ከ3 ቢሊየን ብር በላይ ወጪ የልዩ ልዩ ካፒታል ፕሮጀክቶች ግንባታ እየተካሄደ መሆኑን የክልሉ ፕላንና ልማት ቢሮ አስታወቀ፡፡
ቢሮው ከፕሮጀክት ባለቤት መስሪያ ቤቶች ጋር በጋራ በመሆን በግንባታ ፕሮጀክቶች አፈጻጸም ዙሪያ የድጋፍና ክትትል መርሃ ግብር እያካሄደ እንደሆነ ተመላክቷል።
የቢሮው ምክትልና የማክሮ ኢኮኖሚ እቅድ ዝግጅት ክትትልና ግምገማ ዘርፍ ሃላፊ አቶ ሙባረክ አወል እንዳሉት፥ ከ3 ቢሊየን ብር በላይ ወጪ የክልሉን ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና አስተዳደራዊ እንቅስቃሴዎች የሚያሳልጡ ፕሮጀክቶች ግንባታ እየተካሄደ ነው።
ቢሮውና ባለድርሻ አካላት የእነዚህን ግንባታዎች ጥራትና ደረጃ ለማስጠበቅና በተያዘላቸው ጊዜ አጠናቆ ለአገልግሎት ለማብቃት በቅንጅት እየሰሩ እንደሚገኙም አቶ ሙባረክ ተናግረዋል።
በአሁኑ ወቅት የፕሮጀክት ባለቤት ከሆኑት ውሃ፣ ማዕድንና ኢነርጂ፣ ትራንፖትና መንገድ ልማት፣ ጤና፣ ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮዎች የተውጣጣ የአመራሮችና ባለሙያዎች ቡድን በግንባታ ያሉ የንጹህ መጠጥ ውሃ፣ መንገድና ጤና ተቋማት ፕሮጅክቶችን የአፈጻጸም ደረጃ እየተመለከተ መሆኑንም ከክልሉ የኮሙኒኬሽን ቢሮ የማህበራዊ ትስስር ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.