Fana: At a Speed of Life!

በዳሰነች በኦሞ ወንዝ ሙላት ጉዳት ለደረሰባቸው ትምህርት ቤቶች የ23 ነጥብ 8 ሚሊየን ብር የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ ተደረገ

አዲስ አበባ፣ጥር 17፣2014 (ኤፍ ቢሲ) በደቡብ ኦሞ ዞን ዳሰነች ወረዳ በኦሞ ወንዝ ሙላት ጉዳት ለደረሰባቸው ትምህርት ቤቶች የ23 ነጥብ 8 ሚሊየን ብር የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ ተደረገ።
በደቡብ ክልል በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የማኅበራዊ ክላስተር አስተባባሪ እና የክልሉ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዲላሞ ኦቶሬ፥ የኦሞ ወንዝን ሙላት ተከትሎ የደረሰውን አደጋ ለመቋቋም መንግስት እና መንግስታዊ ያልሆኑ ጅርጅቶች በቅንጅት እየሰሩ ነው ብለዋል።
ዶክተር ዲላሞ፥ በዳሰነች ወረዳ የወደሙ ልዩ ልዩ የመሠረተ ልማት ተቋማትን መልሶ ለማቋቋም የክልሉ መንግስት እንደሚሰራ ጠቁመው፥ የአካባቢው ተማሪዎች በተፈናቀሉበት አካባቢዎች መማር እንዲችሉ ከ2 ሺህ በላይ ድንኳኖች መቅረባቸውንም ጠቁመዋል።
የክልሉ መንግስት ከዩኒሴፍ እና ከዓለም የምግብ ፕሮግራም ጋር በመተባበር ነው በወረዳው የትምህርት ቁሳቁሶች ድጋፍ የተደረገው።
በአካባቢው በውሃ ሙላቱ የተነሳ 12 ትምህርት ቤቶች እና ሦስት የጤና ተቋማት ጉዳት ደርሶባቸዋል።
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.