Fana: At a Speed of Life!

ጀርመን አገራዊ የምክክር ሂደቱን ለመደገፍ ዝግጁ ናት – አምባሳደር ስቴፋን አወር

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 25፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ መንግሥት በኩል ጥያቄ ከቀረበላት ጀርመን አገራዊ የምክክር ሂደቱን ለመደገፍ ዝግጁ መሆኗን በኢትዮጵያ የጀርመን አምባሳደር ስቴፋን አወር ገለጹ፡፡

አምባሳደር ስቴፋን አወር በኢትዮጵያ የሚስተዋሉትን ውስጣዊ ችግሮች በመፍታት መፍትሔ ለማበጀት በጋራ መምከር እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል፡፡

ኢትዮጵያ የምታካሂደው አገራዊ ምክክር ሁሉንም አሳታፊና አካታች ሆኖ ሲካሄድ ልዩነቶችን ተነጋግሮ በመፍታት ብሔራዊ መግባባት መፍጠር እንደሚያስችልም አንስተዋል።

በአገራዊ ምክክሩ ለጋራ ችግሮች መንስኤ የሆኑ ጉዳዮች ምንድን ናቸው? የሚለውን ቁልፍ ጥያቄ በማንሳትና በግልጽ መነጋገር የጋራ መፍትሔ ማምጣት ይቻላል ያሉት አምባሳደሩ ፥ የምክክር ሂደቱን ሁሉን አቀፍ ለማድረግ እየሰራ መሆኑንም አድንቀዋል።

የኢትዮጵያ አገራዊ ምክክር የኢትዮጵያን መሰረታዊ ችግሮች ለመፍታት ጥሩ የመፍትሔ አማራጭ መሆኑን ጠቁመው÷ የፌዴራል ሥርዓት የምትከተለው ጀርመን ከኢትዮጵያ መንግሥት ጥያቄ ከቀረበላት የምክክር ሂደቱን በሚቻለው አቅም ሁሉ ለመደገፍ ዝግጁ እንደሆነች አረጋግጠዋል።

የኢትዮጵያና ጀርመን የሁለትዮሽ ግንኙነት በጠንካራ ወዳጅነት የቀጠለ መሆኑን ያስታወሱት አምባሳደሩ ፥ “ኢትዮጵያ የጀርመን ስትራቴጂካዊ አጋራችን ናት” ሲሉ ተናግረዋል።

በልማት ድጋፍና ትብብር ጀርመን የኢትዮጵያ ዋነኛ አጋር መሆኗን ጠቅሰው ፥ ለዚህም የኢትዮጵያን ዘላቂ ሰላምና መረጋጋት ትሻለች ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

የጀርመን ባለሃብቶች በአገሪቷ በተለያዩ የልማት ዘርፎች መዋዕለ ነዋያቸውን እያዋሉ መሆኑንም አምባሳደሩ ገልጸዋል።

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.