Fana: At a Speed of Life!

በአዲስ አበባ በክፍለ ከተሞች የሚታየው የአገልግሎት አሰጣጥ ክፍተት አሁንም ለነዋሪዎች የቅሬታ ምንጭ ሆኖ መቀጠሉ ተገለፀ

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 1 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ)በአዲስ አበባ በክፍለ ከተሞች የሚታየው የአገልግሎት አሰጣጥ ክፍተት አሁንም ለነዋሪዎች የቅሬታ ምንጭ ሆኖ ቀጥሏል ተባለ፡፡

የመሬትና ይዞታ ነክ ጉዳዮች አገልግሎት መስጫ ጽህፈት ቤቶች ላይ የተገኙ ነዋሪዎች በጽህፈት ቤቶቹ የአገልግሎት አሰጣጥ ላይ የከተማ አስተዳደሩ የተለያዩ ስራዎችን ቢሰራም ቀጣይነት ያለው የተሻሻለ የአገልግሎት ተግባራዊ ሊሆን አልቻለም ብለዋል።

ሰአት አርፍዶ መግባት፣ ውሳኔ ማዘግየት፣ የእውቀትና ክህሎት ችግርና ቅንነት ማጣት በአገልግሎት ሰጪ ሰራተኞቹ ላይ የሚታዩ ባህሪያት መሆናቸውንም ነው ተገልጋዮቹ የጠቆሙት።

አገልግሎት የሚሰጥባቸው አካባቢወች ለተጠቃሚዎች ምቹ አለመሆንን ጨምሮ አገልግሎት ሰጭዎች በስራ ገበታቸው አለመገኘትም ሌላኛው የሚኒሳ ችግር ነው።

ፋና ብርድካስቲንግ ኮርፖሬት በቂርቆስ፣ በየካ እና በልደታ ክፍለ ከተማዎች የመሬት ይዞታና ኤጀንሲ ቅርንጫፍ ተዘዋውሮ ባደረገው ምልከታ የአገልግሎት አሰጣጥ እየተሻሻለ ቢገኝም አሁንም የተገልጋይን እርካታ ማምጣት የሚያስችል የአገልግሎት አሰጣጥ አለመኖሩን ከተገልጋዮች አስተያየት መረዳት ተችሏል።

በአገልግሎት መስጫ ቦታዎች ላይ በቂ ግንዛቤና እውቀት ያላቸውና ቅን ሰራተኞች ቢኖሩ እንዲሁም ጉዳዮች በአንድ መስኮት ማለቅ የሚቻልባቸው መንገዶች ቢዘጋጁ መልካም ነው ሲሉ ተገልጋዮች ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት በሰጡት አስተያየት ተናግረዋል፡፡

 

በትግዕስት ስለሺ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.