በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል 2 ሚሊየን ችግኝ በወጣቶች እንደሚተከል ተጠቆመ
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 8፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በ4ኛው ዙር የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ሁለት ሚሊየን ችግኝ በወጣቶች እንደሚተከል የክልሉ ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ገለጸ፡፡
የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት አደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ አቶ ቀልበሳ ኦልጅራ እንደገለጹት÷ “ለሀገሬ ብልፅግና ዐርበኛ ነኝ” በሚል መሪ ሀሳብ በክልሉ ወጣቶች የበጎ ፈቃድ መርሐ ግብር ለሁለት ወራት ይካሄዳል፡፡
በያዝነው ክረምት በወጣቶች በርካታ ሥራዎች እንደሚሠሩ ጠቁመው÷ ከእነዚህ መካከል አቅመ ደካሞችን መደገፍ አንዱ ነው ማለታቸውን የክልሉ ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት መረጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!