Fana: At a Speed of Life!

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል 2 ሚሊየን ችግኝ በወጣቶች እንደሚተከል ተጠቆመ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 8፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በ4ኛው ዙር የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ሁለት ሚሊየን ችግኝ በወጣቶች እንደሚተከል የክልሉ ብልፅግና ፓርቲ  ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ገለጸ፡፡

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት አደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ አቶ ቀልበሳ ኦልጅራ እንደገለጹት÷ “ለሀገሬ ብልፅግና ዐርበኛ ነኝ” በሚል መሪ ሀሳብ በክልሉ ወጣቶች የበጎ ፈቃድ መርሐ ግብር ለሁለት ወራት ይካሄዳል፡፡

በያዝነው ክረምት በወጣቶች በርካታ ሥራዎች እንደሚሠሩ ጠቁመው÷ ከእነዚህ መካከል አቅመ ደካሞችን መደገፍ  አንዱ ነው ማለታቸውን የክልሉ ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት መረጃ ያመላክታል፡፡

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.