አቶ ኦርዲን በድሪ በኢትዮጵያ ከጀርመን አምባሳደር ጋር የሐረሪ ክልልን የልማት እንቅስቃሴ ለመደገፍ በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ ተወያዩ
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 16፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ ከጀርመን አምባሳደር ስቴፈን አውር ጋር የሀረሪ ክልልን የልማት እንቅስቃሴ በሰው ኃይል ልማትና በቁሳቁስ ለመደገፍ በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ ተወያይተዋል፡፡
ውይይቱን ተከትሎ አቶ ኦርዲን በድሪ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ÷ በኢትዮዽያ ከጀርመን አምባሳደር ስቴፈን አውር ጋር የጀርመን መንግስት እና ግብረ ሰናይ ድርጅቶቹ በተለይም የሰዎች ለሰዎች ድርጅትና ጂ አይ ዜድ የክልሉን የልማት እንቅስቃሴ በሰው ኃይል ልማትና በቁሳቁስ ድጋፍ በሚያደርጉበት ሁኔታ ላይ መክረናል ሲሉ አስፍረዋል፡፡
የጀርመን መንግስት ፣የሰዎች ለሰዎች ድርጅት እና ጂ አይ ዜድ እያደረጉ ላሉት ድጋፍም ምስጋና አቅርበዋል ርዕሰ መስተዳድሩ፡፡
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!