Fana: At a Speed of Life!

በጋምቤላ ክልል አምስት አመራሮች ከኃላፊነታቸው ተነሱ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 16፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በጋምቤላ ክልል ሰሞኑን ሲካሄድ በነበረው የመንግስትና የፓርቲ ግምገማ አምስት የስራ አመራሮች ከኃላፊነታቸው እንዲነሱ መደረጉን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኡሞድ ኡጁሉ ተናገሩ።

የጋምቤላ ክልላዊ መንግስት አስቸኳይ የካቢኔ ስብሰባውን እያካሄደ ሲሆን÷በአስር አጀንዳዎች ዙሪያ ተወያይቶ ውሳኔ ያሳልፋል ተብሎ ይጠበቃል።

ከአጀንዳዎቹ መካከል የ2014 በጀት ዓመት የስራ አፈፃፀም ሪፖርት፣ የ2015 የክልሉ አስፈፃሚ መስሪያ ቤቶች የተጠቃለለ ዕቅድ፣ የተጨማሪ በጀት አዋጅ ቀርቦ ውይይት ይደረግበታል።

በሌላ በኩል ሰሞኑን ለአምስት ተከታታይ ቀናት ሲካሄድ በነበረው የመንግስትና የፓርቲ ግምገማ አምስት የስራ ኃላፊዎች ከኃላፊነታቸው እንዲነሱ መደረጉን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድርና የብልጽግና ፓርቲ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል አቶ ኡሞድ ኡጁሉ ተናግረዋል።

የስራ መሪዎቹ ከኃላፊነታቸው የተነሱት ከህዝብ ጥቅም ይልቅ የግል ጥቅማቸውን በማስቀደማቸውና በፈጸሙት ብልሹ አሰራር መሆኑን አስረድተዋል።

በቀጣይም የድርጅቱ ግምገማና የማጥራት ስራ በዞንና በወረዳዎች እንደሚካሄድ ጠቁመው፥ ተመሳሳይ የእርምት እርምጃዎችም እንደሚወሰዱ ማስታወቃቸውን ከጋምቤላ ክልል የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.