Fana: At a Speed of Life!

ሰላም ለዕድገት ብቻ ሳይሆን እንደ ሀገር ለመቀጠል ወሳኝ ጉዳይ መሆኑ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 16፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ሰላም ለዕድገት ብቻ ሳይሆን እንደ ሀገር ለመቀጠል ወሳኝ ጉዳይ በመሆኑ ልዩነቶችን ማጥበብ፣ መቻቻል፣ መከባበርና መተባበር እንደሚያስፈልግ የሰላም ሚኒስቴር አስታወቀ።

“ከኢድ እስከ ኢድ ጥሪን ተቀብለው የመጡ ዳያስፖራዎች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ ምሁራንና የሚመለከታቸው ተቋማት ተወካዮች የተገኙበት የውይይት መድረክ ዛሬ  ተካሂዷል።

የሰላም ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ታዬ ደንደአ በመድረኩ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት፥ ኢትዮጵያ ካለችበት ተጨባጭ ሁኔታ አንጻር የዳያስፖራው ማህበረሰብ  በሚኖርባቸው ሀገራት ያካበታቸውን የሃይማኖት መቻቻል ተሞክሮዎች በማጋራት ረገድ ያለው ሚና ከፍተኛ መሆኑን ነው የጠቆሙት።

ዳያስፖራው የሃይማኖት መከባበር ተሞክሮዎችን እንደሚያጋራም ያላቸውን እምነት ገልጸዋል።

ዳያስፖራው በሚኖርባቸው ሀጋራት ያሉ ሁኔታዎች ሳይገድቡት ሁልጊዜም ከሀገሩ ጋር ያለውን ትስስር ለማጠናከር የሚያከናውናቸው ስራዎች የሚበረታቱ እንደሆኑም አንስተዋል።

የዳያስፖራ አገልግሎት ምክትል ዋና ዳይሬክተር ዶክተር መሐመድ እንድሪስ በበኩላቸው÷መንግስት ለዘመናት ጸንቶ እንዲቆይ የሀይማኖት ተቋማት የነበራቸውን አስተዋጽኦ አስታውሰው÷ ይህ ዘመናትን የተሻገረ እሴት እያጋጠሙት ያሉ እንቅፋቶችን መሻገር እንዲችል የሚመለከታቸው አካላት የድርሻቸውን ሊወጡ ይገባል ብለዋል።

በኢትዮጵያ የሀይማኖት መከባበርና አብሮነት እንዲጎለብት የኢትዮጵያ የሀይማኖት ተቋማት ጉባኤ ባለፉት 11 ዓመታት ያከናወናቸውን ተግባራት የገለጹት ደግሞ የኢትዮጵያ የሀይማኖት ተቋማት ጉባኤን ወክለው ንግግር ያደረጉት ሀጅ መስኡድ አደም ናቸው፡፡

በመድረኩ ላይ ዳስፖራዎችን ወክለው ንግግር ያደረጉት ኡስታዝ ጀማል በሽር÷ በኖሩባቸው ሃገራት የታዘቡትን የሀይማኖቶች መከባበር ተሞክሮና እንደ ሀገር መወሰድ አለባቸው ያሏቸውን ጉዳዮች በዝርዝር አስረተድተዋል፡፡

መድረኩ ዳያስፖራው ያካበተውን የሀይማኖት መቻቻል ተሞክሮ የሚያካፍልበትን እድል ለመፍጠር ያለመ ነው መባሉን ከዳያስፖራ አገልግሎት የተገኘው መረጃ ያመላክታል፡፡

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.