Fana: At a Speed of Life!

በሶማሌ ክልል አፍዴር ዞን ሾልኮ የገባው አሸባሪው የአልሸባብ ታጣቂ ቡድን ሙሉ ለሙሉ  መደምሰሱን የክልሉ መንግስት ገለጸ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 16፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ከአራት ቀናት በፊት “አቶ” በሚባለው ቦታ ወደ ሶማሌ ክልል አፍዴር ዞን ሾልኮ የገባው የአሸባሪው የአልሸባብ ታጣቂ ቡድን “ሁልሁል” በሚባል ንዑስ ቀበሌ ከተከበበ በኋላ ሙሉ ለሙሉ ለወሬ ነጋሪ ሳይተርፍ መደምሰሱን የክልሉ መንግስት የፀጥታ ምክር ቤት ገልጿል።

የክልሉ ኮሙኒኬሽን እንደገለጸው፥ አሸባሪው ቡድን ወደ አሰበው ቦታ ሳይደርስ ሲጠቀምባቸው የነበሩ 13 ተሽከርካሪዎች የተቃጠሉ ሲሆን፥ ይዞት የገባው ትጥቅና ስንቅም ተማርኳል።

የክልሉ  የፀጥታ ምክር ቤት የሰጠው መግለጫ እንደሚከተለው ቀርቧል።

ከሶማሌ ክልል ፀጥታ ምክር ቤት የተሰጠ መግለጫ!!

ከአራት ቀናት በፊት “አቶ” በሚባለው ቦታ ወደ ሶማሌ ክልል አፍዴር ዞን የገባው አሸባሪው የአልሸባብ ታጣቂ ቡድን “ሁልሁል” በሚባል ንዑስ ቀበሌ ከተከበበ በኋላ ሙሉ ለሙሉ ለወሬ ነጋሪ ሳይተርፍ ተደምስሰዋል።

ቡድኑ በኤልከሬ ወረዳ አልፎ ወደ ኦሮሚያ ክልል በመግባት ከሸኔ ሽብርተኛ ቡድን ጋር ለመገናኘት አልሞ ነበር።

አሸባሪው ቡድን ወደ አሰበው ቦታ ሳይደርስ የያዛቸውን 13 ተሽከርካሪዎች የተቃጠሉ ሲሆን ይዞት የገባው ትጥቅና ስንቅም ተማርኳል።

ለሶስት ቀን በተካሄደው ኦፕሬሽንም ከ100 በላይ የአሸባሪው ቡድን አባላት ተገድለዋል።

ባለፉት ሦስት ቀናት ለኦፕሬሽኑ መሳካት የሶማሌ ክልል ህዝብ እንደ ወትሮው ሁሉ ለጀግናው የሶማሌ ክልል ልዩ  ኃይል የተለያዩ ምግቦች፣ በርካታ የቁም እንስሳቶች፣መጠጦች ፣አልሰባሳት እንዲሁም ደም በመለገስ ከልዩ ሀይሉ ጎን ቆመዋል፣ በመሆኑም የክልሉ ህዝብ ላደረገው ድጋፍና እገዛ የሶማሌ ክልል የፀጥታ ምክር ላቅ ያለ ምስጋና ያቀርባል።

ለኦፕሬሽኑ መሳካት መረጃዎች ለህዝብ ይፋ እንደሚደረጉ የፀጥታ ምክር ቤቱ ያስታውቃል።

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.