Fana: At a Speed of Life!

በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በመደመር መጽሐፍ ላይ ውይይት ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 3፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ በተጻፈው “መደመር” መጽሐፍ ላይ ውይይት ተካሄደ ።

በውይይቱ የዩኒቨርሲቲው አራት ምሁራን ካነበቡት ተነስተው ምሁራዊ ሂስ ሰጥተዋል

በዩኒቨርሲቲው የሰላም እና ደህንነት ጥናት ማዕከል መምህር ዶክተር ዮናስ አዳዬ፣ ዶክተር ያኒያ ሰዒድ ከሶሻል ወርክ ትምህርት ክፍል፣ ዶክተር መሀመድ ሀሰን በዩኒቨርሲቲው የአፍሪካ ጥናት ማዕከል መምህር እንዲሁም ዶክተር ተካልኝ አያሌው የሶሻል አንትሮፖሎጂ መምህር ግምገማቸውን እያቀረቡ ነው።

ዶክተር ዮናስ አዳዬ አሁን ላይ በዓለማችን ከመተባበር ይልቅ መነጠል እየጎላ በመጣበት የመደመር ጽንሰ ሀሳብ መምጣቱ ለችግሩ መፍትሔ ያደርገዋል ብለዋል።

ከሰላም እና ደህነነት አንጻር መፅሃፉ ትልቅ ሀሳብ አንስቷልም ነው ያሉት።

መደመር ሀገር በቀል መሆኑ ለዘላቂ ሰላም ግንባታ መሰረት እንደሚያደርገውም በመድረኩ ላይ ተነስቷል።

ደህንነት የሚከፋፍል አይደለም፤ የአንዱ ሰላም የሌላው ችግሩም የሁሉ ነው ያሉት ዶክተር ዮናስ፥ መደመር ለቀጠናዊ ትብብር ማዕከል ሆኖ እንደሚያገለግል አንስተዋል።

በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በአፍሪካ ጥናት ላይ ተመራማሪ የሆኑት ዶክተር መሐመድ ሀሰን፥ መደመር የኢትዮጵያን የቀደመ የፖለቲካ የጽንፎች ክረት ለማርገብ አማራጭ ሆኖ የተገኘ ነው ብለዋል።

ጸሐፊው በመገዳደል ስልጣን በሚጸናባት ሀገር መግደል መሸነፍ በሚል መምጣታቸው ለአዲስ የፖለቲካ ውይይት በመጽሐፉ በር የከፈተ መሆኑንም አንስተዋል።

መደመር ያለንን አቅም መጠቀም ላይ በማተኮር ለአፍሪካ ችግሮች ምላሽ የማሆን ነው ብለውታል።

የጽንስ ሀሳቡ ውጤት በአፍሪካ ቀንድ በተግባር ታይቷል፤ ለቀጣናው ሰላም እና መረጋጋት የራሱን አስቸዋጽኦ አበርክቷል ተብሏል።

የመደመር እሳቤ በሶሻል አንትሮፖሎጂ ዕይታ በሚል ግምገማቸውን ያቀረቡት ዶክተር ተካልኝ አያሌው መደመር ተራማጅ በመሆኑ ከተለያዪ ጽንሰ ሀሳቦች በጎውን ወስዶ ከኛ እውነታ ጋር ያጣጣመ ነው ብልዋል።

በአላዛር ታደለ

ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!
https://t.me/fanatelevision

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.