ኢትዮጵያ እና የአፍሪካ ልማት ባንክ 44 ነጥብ 4 ሚሊየን ዶላር የድጋፍ ስምምነት ተፈራረሙ
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 20፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ እና የአፍሪካ ልማት ባንክ 44 ነጥብ 4 ሚሊየን ወይንም 2 ነጥብ 3 ቢሊየን ብር የድጋፍ ስምምነት ተፈራረሙ፡፡
የ40 ሚሊየን ዶላር ድጋፉ በአፍሪካ ቀንድ ለምግብና ሥነ-ምግብ ደህንነት ፕሮግራም አፈጻጸም የሚውል ነው ተብሏል፡፡
የ4ነጥብ 4 ሚሊየን ዶላሩ ደግሞ የማክሮ ኢኮኖሚ አስተዳደርን ለማጠናከር ተቋማዊ ድጋፍ ፕሮጀክትን በቅደም ተከተል ለማስፈፀም የሚውል መሆኑን የገንዘብ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል፡፡
በአፍሪካ ቀንድ ለምግብ እና ስነ-ምግብ ደህንነት አቅምን የመገንባት መርሐ ግብር መነደፉ ቀጣይነት ያለው ድርቅን መቋቋም እና የኑሮ ሁኔታን ለማሻሻል የበኩሉን አስተዋፅኦ ለማድረግ አስተዋጽዖ እንዳለው ተገልጿል።
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!