አትሚስ በሚል ስያሜ የተደራጀው የኢትዮጵያ ሰላም አስከባሪ ሰራዊት ቀጠናውን ተረከበ
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 9፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በደቡብ ምዕራብ ሶማሊያ በአሚሶም ሰላም ማስከበር ተልዕኮውን ሲወጣ የነበረው 6ኛው ዙር የኢትዮጵያ ሰላም አስከባሪ ሰራዊት አትሚስ በሚል ስያሜ በአዲስ አደረጃጀት ለተቋቋመው ሰላም አስከባሪ ኃይል አስረከበ፡፡
በርክክብ ስነ ስርዓቱ ላይ በሴክተሩ ስር የሚገኙ ድጋፍ ሰጭ ድርጅቶችና የፀጥታ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።
የሴክተር ሦስት ዋና አዛዥ ብርጋዴር ጄኔራል ዘውዱ ሰጥአርጌ እንደተናገሩት÷ ሴክተሩ ግዳጁን ከተቀበለ ጀምሮ በተሰማራበት የግዳጅ ቀጠና የአካባቢውን ሰላምና ፀጥታ በማረጋገጥ የሶማሊያ ሕዝብ ያለምንም የፀጥታ ስጋት በሰላም ወጥቶ እንዲገባ ማድረግ ችሏል።
በቅርቡም በሶማሊያ ያለምንም የፀጥታ ችግር የተካሄደው ምርጫ አንዱ የሥራችን ውጤት ማሳያ ነው ብለዋል፡፡
የአዲሱ የሴክተር ሦስት የአትሚስ አዛዥ በመሆን ቀጠናውን የተረከቡ ብርጋዴር ጀኔራል በስፋት ፈንቴ÷ በቀጣይ የሥራ ዘመን የተገኙ ጥንካሬዎችን ለማስቀጠል የአትሚስን ተልዕኮ በብቃት እንፈፅማለን ማለታቸውን የመከላከያ ሰራዊት መረጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!