Fana: At a Speed of Life!

የአዲስ አበባ ምክር ቤት መደበኛ ጉባኤ መካሄድ ጀመረ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 4፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) 3ኛው የአዲስ አበባ ምክር ቤት 4ኛ አመት የስራ ዘመን 4ኛ መደበኛ ጉባኤ መካሄድ ጀምሯል።

በጉባኤው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የ2017 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርትና የ2018 በጀት ዓመት እቅድ የትኩረት አቅጣጫዎች ላይ ውይይት እንደሚደረግ ተመላክቷል፡፡

የአስተዳደሩ ዋና ኦዲተር የ2017 በጀት ዓመት የኦዲት ሪፖርትን ማድመጥ እንዲሁም የአስተዳደሩ ፍርድ ቤቶች ዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ላይ ተወያይቶ ማጽደቅ የጉባኤው አጀንዳ ናቸው ተብሏል፡፡

በተጨማሪም የአስፈጻሚ አካላትን ስልጣንና ተግባር እንደገና ለመወሰን የወጣውን አዋጅ ቁጥር 84/2016ን ለማሻሻል የቀረበው ረቂቅ አዋጅ እና የአስተዳደሩ የ2018 በጀት ረቂቅ አዋጅ ላይ ውይይት እንደሚደረግ ተጠቁሟል፡፡

በጉባኤው ማጠቃለያ ምክር ቤቱ ልዩ ልዩ ሹመቶችን እንደሚያፀድቅም ይጠበቃል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.