ወደ መዲናዋ ሊገቡ የነበሩ የጦር መሳሪያዎች ተያዙ
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 11፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ)ትንናት ምሽት ወደ አዲስ አበባ ሊገቡ የነበሩ የተለያዩ የጦር መሳሪያዎች መያዛቸውን የጉምሩክ ኮሚሽን አስታወቀ፡፡
የጦር መሳሪያዎቹ የተያዙት መነሻውን ኮንሶ ባደረገ ላንድ ክሩዘር ተሽከርካሪ 16 ክላንሽኮቭ ፣ ዘጠኝ ምንሽር እና 14 ባዶ ካዝና በተሽከርካሪዉ አካል ላይ በተሰራ ድብቅ አካል (ሻግ) ዉስጥ ተደብቆ ወደ አዲስ አበባ ሊገባ ሲል በቱሉ ዲምቱ ጉምሩክ መቆጣጠሪያ ጣቢያ ነው፡፡
የጦር መሳሪያውን ሲያዘዋውሩ የተገኙ ሶስት ተጠርጣሪዎችም በቁጥጥር ስር መዋላቸው የተገለፀ ሲሆን ÷የጦር መሳሪያው ወደ አዲስ አበባ ቢገባ ከፍተኛ ጥፋት የሚያደርስ መሆኑን ከጉምሩክ ኮሚሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
የኮንትሮባንድ እና ህገወጥ ንግድን ለመግታት፣ በሀገር ኢኮኖሚ የሚያሳድረውን አሉታዊ ተጽእኖ ለመከላከል ሁሉም የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣ ኮሚሽኑ ጥሪ አቅርቧል፡፡
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!