Fana: At a Speed of Life!

የሶማሊያ ጦር የሞቃዲሾ የሆቴል ከበባ ማብቃቱን አስታወቀ

አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 15 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሶማሊያ ጦር በመዲናዋ ሞቃዲሾ በሚገኝ ሆቴል ገብተው ጥቃት የፈጸሙ ታጣቂዎችን ድል ማድረጉን አስታወቀ።

ሐያት በተባለው ሆቴል ታጣቂዎች በፈጸሙት ጥቃት 21 ሰዎች ለህልፈት ሲዳረጉ በርካታ ሰዎችም ቆስለዋል ነው የተባለው።

ከጥቃቱ በኋላም ታጣቂዎቹ ሆቴሉን በመክበብ ከፀጥታ ሃይሎች ጋር የተኩስ ልውውጥ ማድረጋቸው ተገልጿል።

የሃገሪቱ ጦርም 30 ሰአታት የፈጀው ከበባ ማብቃቱን እና ታጣቂዎቹን ድል ማድረጉን አስታውቋል።

ታጣቂዎቹ ከትናንት በስቲያ ተቀጣጣይ ፈንጂዎችን በመጠቀም ወደ ሆቴሉ ከገቡ በኋላ የሆቴሉን እንግዶች አግተው ነበር።

ከበባውን እና የታገቱ እንግዶችን ለማስለቀቅ በተደረገው የተኩስ ልውውጥ የሆቴሉ አብዛኛው ክፍል መውደሙን ቢቢሲ እና አልጀዚራ በዘገባቸው አመላክተዋል።

ለጥቃቱ አልሸባብ ሃላፊነቱን እንደሚወስድ ገልጿል።

የአርብ ዕለቱ ጥቃት ሀሰን ሼክ መሀሙድ የሶማሊያ ፕሬዚዳንት ሆነው ከተመረጡ በኋላ አልሸባብ በሞቃዲሾ የፈጸመው የመጀመሪያው ሆኖ ተመዝግቧል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.