Fana: At a Speed of Life!

ሱዳን የጎርፍ አደጋ የጥንቃቄ እና የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አወጀች

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 16፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ሱዳን በስድስት ተጋላጭ ግዛቶች የጎርፍ አደጋ የጥንቃቄ እና የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አውጃለች፡፡

የሱዳን የሚኒስትሮች ምክር ቤት ባደረገው ስብሰባ በናይል ወንዝ፣ ገዚራ፣ ነጭ አባይ፣ ምዕራብ ኮርዶፋን፣ ደቡብ ዳርፉር እና ከሳላን ጨምሮ በስድስት ግዛቶች የጥንቃቄ እና የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አውጇል፡፡

ውሳኔው የተላለፈው በሱዳን የተለያዩ አካባቢዎች ከዚህ በፊት ታይቶ የማይታወቅ ከባድ ዝናብ እና የጎርፍ መጥለቅለቅ እየተስተዋለ መምጣቱን ተከትሎ መሆኑ ተገልጿል፡፡
የሱዳን ሲቪል ጥበቃ ብሄራዊ ምክር ቤት እሁድ እለት ባወጣው ሪፖርት በጎርፍ አደጋ እስካሁን 80 ሰዎች ለህልፈት መዳረጋቸውን አስታውቋል።

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ባወጣው ሪፖርት ደግሞ ከሰኔ ወር ጀምሮ 136 ሺህ ሱዳናውን በጎርፍ አደጋው ተጠቂ እንደሆኑ መግለጹን ሲ ጂ ቲ ኤን እና ሱና ኒውስ ዘግበዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.