በ2014 በጀት ዓመት ከአምራች ዘርፉ የተሻለ ውጭ ምንዛሬ ገቢ ተመዝግቧል – አቶ መላኩ አለበል
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ19፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በ2014 በጀት ዓመት ከአምራች ዘርፉ የተሻለ ውጭ ምንዛሬ ገቢ የተመዘገበበት ነው ሲሉ የኢንዱስትሪ ሚኒስትር አቶ መላኩ አለበል ገለጹ፡፡
የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር በ2014 በጀት አፈጻጸም ፣ 2015 ዕቅድ ዝግጅትና ኢትዮጵያ ታምርት ሀገራዊ ንቅናቄ ላይ ውይይት እያካሄደ ነው፡፡
በተጠናቀቀው በጀት ዓመት የዘርፉን የወጪ ንግድ ማሳደግ፣ ገቢ ምርት በአገር ውስጥ መተካት፣ የማምረት አቅምና አጠቃቀምን ማሻሻል እንዲሁም የስራ እድል ፈጠራ ትኩረት ተሰጥቷቸው ሲሰሩ ከነበሩ ስራዎች መካከል ዋና ዋናዎቹ መሆናቸውን ሚኒስትሩ ገልጸዋል፡፡
በዚህም ከዘርፉ ከ500 ሚሊየን በላይ የአሜሪካን ዶላር የተመዘገበበት፣ ከ2 ቢሊየን በላይ ዋጋ ያላቸው ምርቶች በአገር ውስጥ መተካት የተቻለበት፣ አጠቃላይ የማምረት አቅም 52 በመቶ ማድረስ የተቻለበትና ነባርና አዳዲስ ኢንቨስትመንቶችን በማስፋፋትና በማጠናከር ከ258 ሺህ በላይ የስራ እድል አማራጮች የተፈጠረበት ነው ብለዋል፡፡
በቀጣይም የ2015 ዕቅድ መሳካት የሁሉንም አንድነት ትብብርና ቅንጅት ይጠይቃልም ብለዋል ሚኒስትሩ፡፡
በዕቅድ የተያዙትን ግቦች ለማሳካት ሁሉም ፈጻሚ የበኩሉን ሚና እንዲወጣ ጥሪያቸውን ማስተላለፋቸውን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!