የብሪታንያው “ዩኒሊቨር” ኩባንያ በኢትዮጵያ በምግብ ማቀነባበር ዘርፍ መሰማራት እንደሚፈልግ ገለጸ
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 19፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በለንደን የሚገኘው “ዩኒሊቨር” የተባለው ኩባንያ በኢትዮጵያ የምግብ ማቀነባበር ዘርፍ ለመሰማራት ፍላጎት እንዳለው አስታወቀ፡፡
በእንግሊዝ የኢትዮጵያ ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ተፈሪ መለሰ ከዩኒሊቨር ኩባንያ የአፍሪካ ኮርፖሬት ጉዳዮች ዳይሬክተር ዳጊ በሩ ጋር ተወያይተዋል፡፡
በውይይታቸውም÷ መንግስት ቅድሚያ በሰጠው የግብርና ማቀነባበር ዘርፍ ለሚሰማሩ የውጪ ባለሃብቶች በሚሰጠው ማበረታቻ ዩኒሊቨር ኩባንያ ተጠቃሚ እንደሚሆን ተገልጿል፡፡
ኩባንያው በምግብ ማቀነባበር ኢንቨስትመንት ላይ ለመሰማራት ላቀረበው ጥያቄ አስፈላጊው ሁሉ ድጋፍ እንደሚደረግ አምባሳደር ተፈሪ መናገራቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ አመላክቷል፡፡
የዩኒሊቨር የአፍሪካ ኮርፖሬት ጉዳዮች ዳይሬክተር ዳጊ በሩ በበኩላቸው÷ ኩባንያቸውበኢትዮጵያ ባለፉት ዓመታት በተለያዩ የማምረቻ ዘርፎች መሰማራቱን አስታውሰዋል፡፡
በቀጣይም ከሌሎች የውጭ ባለሃብቶች ጋር በመቀናጀትም ሆነ በተናጠል በኢትዮጵያ የምግብ ማቀነባበር ለመሰማራት ዝግጅት እያደረጉ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!