የድሬዳዋ አስተዳደር እና የአሜሪካ ኤምባሲ በጋራ በሚሠሩባቸው ጉዳዮች ላይ መከሩ
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 19፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ጁሃር ከድር እና በኢትዮጵያ የአሜሪካ ኤምባሲ ጉዳይ ፈጻሚ አምባሳደር ትሬሲ አን ጃኮብሰን በጋራ በሚሠሩባቸው ጉዳዮች ላይ ተወያይተዋል፡፡
ከንቲባ ከድር ጁሃር በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሑፍ÷ በጤና፣ በትምህርትና ሌሎች ዘርፎች በጋራ መሥራት በሚችሉባቸው ሁኔታዎች ላይ መወያየታቸውን ገልፀዋል፡፡
በኢትዮጵያ የአሜሪካ ኤምባሲ ጉዳይ ፈጻሚ አምባሳደር ትሬሲ አን ጃኮብሰን “ግብዣዬን ተቀብለው ወደ “ትንሿ ኢትዮጵያ” ድሬዳዋ በመምጣታቸው ደስ ብሎኛል” ብለዋል ከንቲባ ከድር፡፡
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!