Fana: At a Speed of Life!

ህወሓት የሰብዓዊ እርዳታ አቅርቦት ሥራዎችን እንዲያከብር ሳማንታ ፓወር አሳሰቡ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 20፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ህወሓት የዘረፈውን ነዳጅ እንዲመልስና የሰብዓዊ ድጋፍ ሥራዎችን እንዲያከብር የአሜሪካ ተራድዖ ድርጅት (ዩ ኤስ ኤይድ) ኃላፊ ሳማንታ ፓወር አሳሰቡ፡፡

ኃላፊዋ በትዊተር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት፥ ህወሓት የፈፀመውን የነዳጅ ስርቆትና በእርዳታ ሠራተኞች ላይ ያደረሰውን እንግልት በፅኑ አውግዘዋል፡፡

በጦርነቱ ጉዳት የደረሰባቸውን ኢትዮጵያውያን ለመርዳት የሚደረገውን እንቅስቃሴ ማደናቀፍ  ጨካኝ  ድርጊት  ነው ብለዋል፡፡

ህወሓት የዘረፈውን ነዳጅ እንዲመልስና የሰብዓዊ ድጋፍ ሥራዎችን እንዲያከብር ኃላፊዋ አሳስበዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.