Fana: At a Speed of Life!

በርዕሰ መስተዳድር ኦርዲን በድሪ የተመራ ልዑክ በኔዘርላንድስ የሥራ ጉብኝት አደረገ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 14፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በሐርሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ኦርዲን በድሪ የተመራ ልዑክ በኔዘርላንድስ የሥራ ጉብኝት አድርጓል፡፡
 
ልዑካኑ በኢትዮጵያ የተለያዩ የንጽህ መጠጥ ውሃ ፕሮጀክቶች ግንባታ ላይ በሚሳተፈው ቫይተንስ ኢቪደስ በተሰኘ ፋውንዴሽን ግብዣ ነው በኔዘርላንድስ የስራ ጉብኝት ያደረገው፡፡
 
ልዑካኑ በኔዘርላንድስ ቆይታው ከፋውንዴሽኑ ጋር በውሃ ዘርፍ ያላቸውን ትብብር ማጠናከር በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ መክሯል፡፡
 
በሌላ በኩል የልዑካኑ ቡድኑ አባላት በቤልጂየም የኢትዮጵያ አምባሳደር ሂሩት ዘመነ ጋር በተለያዩ ጉዳዮች ላይ መወያየታቸውን ከኤምባሲው ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
 
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.