ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከካናዳው ጠቅላይ ሚኒስትር ጋር በስልክ ተወያዩ
አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 14 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከካናዳው ጠቅላይ ሚኒስትር ጀስቲን ትሩዶ ጋር በስልክ ተወያይተዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከትሩዶ ጋር ውጤታማ ውይይት ማድረጋቸውን አስታውቀዋል።
በውይይታቸውም የሀገራቱን የሁለትዮሽ ግንኙነት ማጠናከር በሚቻልበት አግባብ ላይ መምከራቸውን ጠቁመዋል።