Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያና የተባበሩት አረብ ኢሚሬቶች በመከላከያ ኢንዱስትሪ ልማት በጋራ ለመሥራት ተሥማሙ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 13፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያና የተባበሩት አረብ ኢሚሬቶች በመከላከያ ኢንዱስትሪ ልማት እና ኢንቨስትመንት መሥኮች በጋራ ለመሥራት ተሥማሙ፡፡
በመከላከያ ሚኒስትር አብረሃም በላይ እና በመከላከያ ሠራዊት ምክትል ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ጄኔራል አበባው ታደሠ የተመራ ልዑክ የመከላከያ ዓለምአቀፍ አውደርዕይና ኮንፈረንስ ላይ ለመሳተፍ አቡዳቢ ገብቷል::
በቆይታቸው ከተባበሩት ዓረብ ኢሚሬቶች ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ሼክ መንሱር ቢን ዛይድ አልናህያን፣ ከመከላከያ ጉዳዮች ሚኒስትር ዲኤታ መሃመድ አህመድ አልባዋዲ፣ ከጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ሌተናል ጄኔራል ኢሳ ሴይፌ መሃመድ አልመዙሪ እና ከምክትል ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ሜጄር ጄኔራል ሼክ አህመድ ቢን ታህኑን አልናህያን ጋር ባደረጉት ውይይት በሀገራቱ መካከል የነበሩ ትብብሮችን ይበልጥ ማጠናከር በሚቻልበት ሁኔታ መክረዋል፡፡
የመከላከያ ኢንዱስትሪ የልማት እና ኢንቨስትመንት ስራዎች በተቋሙም ሆነ በኢትዮጵያ ላይ ያለውን ዘላቂ ጠቀሜታ በመገንዘብ የመልካም ተሞክሮ ልውውጥ ከማድረግ ባሻገር ይበልጥ ማሥፋት በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ተወያይተዋል::
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.