Fana: At a Speed of Life!

በ1 ነጥብ 5 ቢሊየን ብር ወጪ የተገነባው “ስቴይ ኢዚ” ሆቴል ተመረቀ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 28፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ ጉለሌ ክፍለ ከተማ አዲሱ ገበያ አካባቢ በ1 ነጥብ 5 ቢሊየን ብር ወጪ የተገነባው “ስቴይ ኢዚ” ባለ 5 ኮከብ ሆቴል ተመረቀ፡፡

ሆቴሉ÷ 103 የመኝታ ክፍሎች፣ ሥድስት ከ 10 እስከ 100 ሰዎች የሚይዙ የስብሰባ አዳራሾችን እና ሦስት ባርና ሬስቶራንቶችን ያካተተ ነው፡፡

የአዲስ አበባ ከተማን በሦስቱም አቅጣጫ እንዲያሳይ ተደርጎ መገንባም ተገልጿል፡፡

በምረቃ ሥነ ስርዓቱ የቱሪዝም ሚኒስትር ዲኤታ ስለሺ ግርማ ባደረጉት ንግግር÷ ሆቴሉ በተለያየ ምክንያት ተቀዛቅዞ የነበረውን የሆቴል እና ቱሪዝም እንቅስቃሴ በማነቃቃት ረገድ ሚናው የጎላ ነው ብለዋል።

ከንግድ በዘለለ ማህበራዊ ኃላፊነትን ለመወጣት የከርሰ ምድር ውኃ በማውጣት ለአካባቢው ማሕበረሰብ በነፃ እንዲጠቀሙ እየተደረገ መሆኑን የሆቴሉ ባለቤት ሕይወት አየለ ተናግረዋል፡፡

ሆቴሉ ለ250 ሰዎች የሥራ ዕድል መፍጠሩንም ነው የገለጹት፡፡

በቀጣይም በቀን ከ30 እስከ 40 ሺህ ዳቦ በማምረት ለአካባቢው ማሕበረሰብ በተመጣጣኝ ዋጋ ለማቅረብ ዝግጅት መደረጉን ጠቁመዋል፡፡

በታሪኩ ወ/ሰንበት

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.