Fana: At a Speed of Life!

ከ214 ሚሊየን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ እቃዎች ተያዙ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 7፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የጉምሩክ ኮሚሽን ከሚያዝያ 27 እስከ ግንቦት 3 ቀን 2015 ዓ.ም ባደረገው ክትትል ከ214 ሚሊየን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ እቃዎች መያዙን አስታወቀ፡፡

174 ነጥብ 9 ሚሊየን የገቢ የኮንትሮባንድ እቃዎች እና 39 ነጥብ 6 ሚሊየን ብር የውጭ በድምሩ 214 ነጥብ 6 ሚሊየን ብር በላይ የሚያወጡ የኮንትሮባንድ እቃዎች ናቸው በተለያዩ ቅርንጫፍ ጽ/ ቤቶች የተያዙት፡፡

ከተያዙት እቃዎች መካከልም አልባሳት፣ ነዳጅ፣ የቁም እንስሳት፣ ኤሌክትሮኒክስ፣ ቡና፣ መድሃኒት፣ ተሽከርካሪዎች፣ የመዋቢያ እቃዎች የጦር መሳሪያዎች፣ ጫት፣ አደንዛዥ ዕጾች፣የምግብ ዘይት እና የተለያዩ ሀገር ገንዘቦች ይገኙበታል፡፡

አዲስ አበባ ድሬድዋ ፣ ሀዋሳ እና ሞያሌ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቶች ደግሞ የኮንትሮባንድ እቃዎቹን በመያዝ ከፍተኛውን ድርሻ እንደሚወስዱ የኮሚሽኑ መረጃ ያመላክታል፡፡

የኮንትሮባንድ እና ሕገወጥ ንግድን በመከላከል ረገድ ባላድርሻ አካላትና ህብረተሰቡ በኩሉን ድርሻ እንዲወጣም ጥሪ ቀርቧል፡፡

#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.