Fana: At a Speed of Life!

አቶ ደመቀ መኮንን የግብርና ሳይንስ አውደ ርዕይን ጎበኙ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 15፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን በሳይንስ ሙዚየም የተዘጋጀውን የግብርና ሳይንስ አውደ ርዕይ ጎበኝተዋል።

አቶ ደመቀ መኮንን በጉብኝት ወቅት እንዳሉት÷ እንደ ሀገር ግብርናውን ለማዘመን በርካታ ስራዎች እየተሰሩ ነው፡፡

በዚህም ውጤት እየተመዘገበ መሆኑን ነው የተናገሩት፡፡

አቶ ደመቀ በአውደ ርዕዩ በአማራ ክልል እየተሰሩ ያሉ የግብርና ስራዎችን እንደተመለከቱ ጠቁመው÷ በዚህም ግብርናው ምን ደረጃ ላይ እንዳለ ለማየት ችለናል ብለዋል፡፡

ዝርያን ለማሻሻልና ምርትና ምርታማነትን ለመጨመር በሰብል ልማት፣ በእንስሳት ሃብትና መሰል ምርቶች የተመለከትነው ነገር የሚበረታታና ተስፋ ሰጭ እንደሆነም አስረድተዋል።

በአሁኑ ወቅት በአማራ ክልል ለብዙ ዓመታት ሲሰራበት የኖረው የግብርና አስተራረስ ዘዴን ለማዘመን እየተሰራ ያለው ስራ በክልሉ ምርትና ምርታማነት ላይ ተጨባጭ ለውጥ እያመጣ መሆኑንም ገልጸዋል፡፡

እንደሀገር በቀጣይ በግብርናው ዘርፍ መልካም ውጤቶች እንደሚመዘገቡ መናገራቸውንም የግብርና ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.