Fana: At a Speed of Life!

አቶ ሙስጠፌ ከአውበሬ፣ ሀረዋና ደንበል ወረዳ ነዋሪዎች ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 17፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፌ መሃመድ በክልሉ ከአውበሬ፣ ሀረዋና ደንበል ወረዳ ከሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎች ጋር በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ተወያዩ፡፡
 
ርዕሰ መስተዳድሩና ልዑካቸው ከውይይቱ በፊት በሀረዋ ወረዳ የሚገኙ የግብርና ምርትና ምርታማነት ፣የትምህርት፣ የጤና ፣ የመንገድና የንጹህ መጠጥ ውሃ መሰረተ ልማቶችን ጎብኝተዋል፡፡
 
በወረዳው በ45 ሚሊየን ብር ውጪ ለሚገነባው የቡላሌ-አንተር-ሀረዋ መንገድ ፕሮጀክት ግንባታም የመሰረት ድንጋይ አስቀምጠዋል።
 
በተጨማሪም በደምበል ወረዳ የሚገኘውን የአራቢ ቀበሌ ፍል ውሃና የቱሪዝም መስህብ የጎበኙ ሲሆን÷ መስህቡ ለቱሪዝሙ ካለው ጥቅም እንፃር ጥናትና ምርምር እንዲደረግበት አሳስበዋል።
 
በመጨረሻም መንግሥት በወረዳዎቹ የህዝቡ የመሰረተ ልማት ጥያቄዎችን በተገቢው መንገድ ምላሽ እንደሚሰጥ መናገራቸውን ከክልሉ ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.