Fana: At a Speed of Life!

የጄኖአ ግዛት ባለሃብቶች በኢትዮጵያ በታዳሽ ኃይልና አበባ ምርት ለመሰማራት ፍላጎታቸውን ገለጹ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 23፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በጣሊያን የኢትዮጵያ አምባሳደር ደሚቱ ሀምቢሳ በጄኖአ ግዛት ከተለያዩ የኢንዱስትሪ ዘርፍ አመራሮች ጋር ተወያይተዋል፡፡
 
በውይይታቸውም አምባሳደር ደሚቱ በኢትዮጵያ ስላለው ምቹ የኢንቨስትመንት እና የገበያ እድል ገለጻ አድርገዋል፡፡
 
በኢትዮጵያ የውጭ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንት ሕግ እና አሰራር ዙሪያም ማብራሪያ የሰጡ ሲሆን÷ ከተሳታፊዎች ለተነሱ ጥያቄዎችም ምላሽ ሰጥተዋል፡፡
 
በመድረኩ የጄኖአ ግዛት ኢንዱስትሪ ማህበር ተወካዮች በኢትዮጵያ በሽርክና አሰራር በታዳሽ ኃይል፣ አበባ ምርትና አግሮ-ኢንዱስትሪ ለመስራት ፍላጎት ማሳየታቸውን የኤምባሲው መረጃ ያመላክታል፡፡
 
በቀጣይ የኢትዮጵያን ቡና የሚያስተዋወቅ መድረክ እንደሚያዘጋጁ ጠቁመው÷ በዘርፋ የሚሰሩ ኢትዮጵያውያንም እንዲሳተፉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.