Fana: At a Speed of Life!

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በኢጋድ አባል ሀገራት መደበኛ ጉባኤ ለመሳተፍ ጅቡቲ ገቡ

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 5 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እና ልዑካን ቡድናቸው በኢጋድ አባል ሀገራት መደበኛ ጉባኤ ለመሳተፍ ጅቡቲ ገብተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በ14ኛው የምሥራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግሥታት (ኢጋድ) አባል ሀገራት ርዕሳነ ብሔራት እና መንግሥታት መደበኛ ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ ነው ጅቡቲ የገቡት።

በጉባኤው የኢጋድ አባል ሀገራት መሪዎች እና ባለስልጣናት የሚሳተፉ ሲሆን ቀጣናዊ ተቋሙ በምስራቅ አፍሪካ እየተከናወኑ ላሉ ስራዎች እየሰጠ ባለው ምላሽን ቀጣናዊ ጉዳዮች ላይ እንደሚመክሩ ይጠበቃል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.