በኦሮሚያ ክልል ከ127 ሺህ የሚልቁ ሕገወጥ የንግድ ድርጅቶች መኖራቸው ተመለከተ
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 8፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በኦሮሚያ ክልል ከሚገኙ 803 ሺህ የንግድ ድርጅቶች መካከል ከ127 ሺህ በላይ የሚሆኑት ሕገወጥ መሆናቸውን የክልሉ ንግድ ቢሮ አስታወቀ፡፡
የቢሮው ምክትል ኃላፊ ተስፋዬ ጎሾ በሰጡት መግለጫ÷ ክትትል እና ቁጥጥር ከተደረገባቸውከ803 ሺህ በላይ የንግድ ድርጅቶች መካከል 127 ሺህ 920 ሕገ ወጥ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡
የዋጋ ንረትን ለማረጋጋት በየቦታው የቅዳሜ ገበያዎችን ማጠናከር ወሳኝ ስለመሆኑም አንስተዋል፡፡
በተለያዩ ከተሞችና ወረዳዎች የቅዳሜ ገበያ መቋቋሙን ጠቁመው÷ የገበያ ማረጋጋት ኮሚቴ ተግባራትን በማጠናከር እና ከሴክተሮች ጋር በቅንጅት በመሰራቱ ውጤት መገኘቱን ተናግረዋል፡፡
በገመቹ ቤኩማ