Fana: At a Speed of Life!

የአፍሪካ የድንበር ተሻጋሪ ወንዞች ከፍተኛ የሚኒስትሮች ስብሰባ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 15 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የአፍሪካ የድንበር ተሻጋሪ ወንዞችን በእኩልነትና በምክንያታዊነት መጠቀም የሚያስችል ሁለተኛው ከፍተኛ የሚኒስትሮች ስብሰባ በአዲስ አበባ መካሄድ ጀምሯል፡፡

ስብሰባው “የእኩል ምክንያታዊ የድንበር ተፋሰስ ወንዞች ተጠቃሚነት ለአፍሪካ ብልፅግና ወሳኝ” ነው በሚል መሪ ሃሳብ ነው እየተካሄደ የሚገኘው።

የጉባዔው ተቀዳሚ ዓላማ የአባይን ወንዝ ፍትሃዊና ምክንያታዊ በሆነ መንገድ ለመጠቀም የሚያስችል የልምድ ልውውጥ ለማድረግ መሆኑ ተመላክቷል፡፡

በተጨማሪም በጉባኤው የድንበር ተሻጋሪ ወንዞችን በማልማት ረገድ የሳንይሳዊ ጥናትና ምርምሮችን እንዲሁም የወንዞችን የፍትሃዊ ተጠቃሚነት መርህን አስፈላጊነት በተመለከተ ምክክር እንደሚደረግ ተመላክቷል፡፡

በመድረኩ የኢፌዴሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ጨምሮ ከናይል ተፋሰስ ሀገራት የተውጣጡ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች እየተሳተፉ ይገኛሉ፡፡

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.