አቶ ደመቀ መኮንን የድሬዳዋ ነፃ የንግድ ቀጠናን ጎበኙ
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 19፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን በድሬዳዋ ከተማ የሚገኙትን የድሬዳዋ ነፃ የንግድ ቀጠና፣ የድሬዳዋ ደረቅ ወደብ እና ድሬዳዋ ሞተርስን ጎብኝተዋል።
የቢዝነስ ተቋሞቱ በዋናነት ÷ በመኪና መገጣጠም፣ በጨርቃ ጨርቅ፣ ፕላስቲክ እና ባለ ሶስት እግር ተሽከርካሪ በማምረት ላይ የተሰማሩ መሆናቸው ተገልጿል፡፡
የባቡር አገልግሎት በአዲስ እና በዘመነ ሁኔታ ተገንብቶ ስራ መጀመሩ ድሬዳዋን ለቢዝነስ ተቋማት ተመራጭ ማድረጉ ተጠቁሟል፡፡
በተጨማሪም ከወደብ በቅርብ እርቀት ላይ መገኘቷ ሌላው መልካም አጋጣሚ መሆኑም ነው የተመለከተው፡፡
በጉብኝቱ ወቅት የድሬዳዋ ምክትል ከንቲባ እና ንግድና እንዱስትሪ ቢሮ ኃላፊ ሀርቢ ቡህ እንዲሁም የከተማዋ የተለያዩ የስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።