የ12ኛ ክፍል 2ኛ ዙር ተፈታኞች ወደተመደቡበት ዩኒቨርሲቲ እየገቡ ነው
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 23፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የ12ኛ ክፍል ሁለተኛ ዙር ሀገር አቀፍ ፈተና የሚወስዱ ተማሪዎች ወደ ተመደቡበት ዩኒቨርሲቲ እየገቡ ነው፡፡
የ2ኛው ዙር (የተፈጥሮ ሣይንስ) ተፈታኝ ተማሪዎች ፈተና ወደሚወስዱበት ዩኒቨርሲቲ ማቅናት የጀመሩት ትናንት ሲሆን ዛሬም ቀጥሎ ውሏል፡፡
በነገው ዕለትም ለተፈታኞች ገለጻ (ኦሬንቴሽን) እንደሚሰጥ ነው የተገለጸው፡፡
ፈተናውም ከማክሰኞ እስከ ዓርብ ድረስ ይሰጣል መባሉን የወጣው መርሐ ግብር ያመላክታል፡፡
ባሳለፍነው ሣምንት የመጀመሪያው ዙር (የማኅበራዊ ሣይንስ) ፈተና መሰጠቱ ይታወቃል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!